አሥራ ስምንቱ የመማክርት ጉባኤው አማካሪዎች ከፊሉ የተሳተፉባቸው ሁለት መድረኮች መሰንበቻውን ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተስተናግደዋል።
በአካባቢው ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ጋር የተወያይው ምክር ቤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚያስችል ፈቃድ የሚያገኝበትን ሕጋዊ ሕልውና ጨምሮ ሥራውን በብቃት ለማከናወን የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን አስታውቋል።
የድርጅቱን የዕለት-ተዕለት ሥራ የሚያስፈጽምና በዲሬክተሮች ቦርድ የሚመራ ጽ/ቤት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ የሚሰበሰበው የአደራ ገንዘብ ለምን ዓይነት ሥራዎች እንደሚውል ስለሚታቀድበት ግልጽነትና ተዓማኒነት ያለው አሠራር፤ ስለ ወጣቶች የጎላ ተሳትፎና በቴክኖሎጂ የሚደገፉ አዳዲስ ቀልጣፋ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ ያላቸውን ውጥን አስመልክቶ ገለጻ አድርጓል።
በረሃብና ቸነፈር የሚሰቃዩ ሕጻናትን እምባ ለማበስ በአንድ ብር እርዳታ ተፈትነናል” ሲል የጥያቄውን ምንነት ያስረዳው ደግሞ በጋዜጣዊ መግለጫው ከተሳተፉት የአማካሪ ቡድኑ አባላት አንዱ አርቲስት ታማኝ በየነ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ