በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'ከናዝሬት መልካም ነገር አይወጣም' የሚሉ ካሉ ተሣስተዋል - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ


ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ - የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር
ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ - የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

የኢሕአዴግን የሁለት ሣምንታት ግምገማ ተከትሎ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎችና በሌሎችም አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ሰሞኑን 528 እሥረኞችን ለቅቃለች። በመጭዎቹ ሁለት ወራት ውስጥም ተመሣሣይ እርምጃ እንደሚቀጥል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ ተናግረዋል።

የኢሕአዴግን የሁለት ሣምንታት ግምገማ ተከትሎ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎችና በሌሎችም አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ኢሕአዴግ ከሁለት ሣምንታት ግምገማው በኋላ የደረሰበት አቋም የተስፋ ብቻ ሳይሆን በተከታታይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌሎችም ወገኖች አብሮ ለመሥራት “መጓዝ የሚገባቸውን ርቀት መሄድ ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

ከዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

'ከናዝሬት መልካም ነገር አይወጣም' የሚሉ ካሉ ተሣስተዋል - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:30 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG