በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኮሮና ያልተበገረው ወጣቱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ


ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ከበሽታው ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ሌሎች የጎንዮሽ ችግሮች እንደሚጋለጡ በጤናው ዘርፍ የሚወጡ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ከነዚህ ችግሮች አንዱ አብዝቶ ከመጨነቅ የሚመጣ የአይምሮ ጤና እክል አንዱ ሲሆን ተመራማሪዎች ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የአይምሮ መረበሽ፣ የእንቅልፍ ማጣትና ነገሮችን በትኩረት አለማሰብ የመሳሰሉ ችግሮች እንደሚገጥማቸው አሳውቀዋል። የዛሬ አምስት ወር አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ካደረሰበት ፅኑ ህመም ያገገመው ወጣት ፍፁም ፀጋዬ ግን ከበሽታው ከዳነ በኃላ ባሳለፋቸው ጥቂት ወራት ህፃናትን የአማርኛ ቋንቋ ለማስተማር የሚረዱ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶችን (መተግበሪያዎችን) እየሰራ ለተጠቃሚው በነፃ ያቀርባል። ወጣቱ ቫይረሱ ስላደረሰበት ፅኑ ህመምና ከህመሙ ካገገመ በኋላ እየሰራቸው ሳላሉት የፈጠራ ውጤቶች ዙሪያ አነጋግረነዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለኮሮና ያልተበገረው ወጣቱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00


XS
SM
MD
LG