ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ቁጥሩ በእጅጉ እያሻቀበ የመጣው ስርጭት የደቀነውን ፈተናው እና ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች አስመልክቶ ከሶስት ከፍተኝ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር የተጀመረ ተከታታይ ውይይት ነው።
ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ባለፈው ዓመት በወረርሽኙ ክፉኛ በተጠቁ አገሮች መጀመሪያ ሰሞን የታየውን በብርቱ ፈተናዎች የታጀበ ሁኔታ በማዛመድ በተለይ ለዛሬው የኢትዮጵያ ይዞታ የሚበጁ የሚባሉ አማራጮችም በውይይቱ ይነሳሉ።
ተወያዮች፦ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ በኢትዮጵያ የጸረ ኮቪድ 19 ዘመቻ በንቃት ከሚሳተፉ በርካታ ታዋቂ የህክምና ባለሞያዎች ውስጥ ሶስቱ ዶ/ር እናውጋው መሃሪ ዶ/ር አሰፋ ጄጃው መኮንን እና ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ናቸው።