በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ማህበረሰባዊ ድርጅቶች ኔትዎርክ መግለጫ አወጡ


“የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች ኔትዎርክ በሚል በመላው ዓለም የተሰባሰቡ 50 የኢትዮጵያውያንና የትውልደ- ኢትዮጵያውያን የሲቪክ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ህግን በማስከበርና በአባይ ጉዳይ ያሳየውን አቋም በመደገፍ መግለጫ አውጥተዋል ”

“እኛ ከ50 በላይ የምንሆን በመላው ዓለም ተሰራጭተን የምንገኝ የኢትዮጵያውያንና የትውልደ- ኢትዮጵያውያን የሲቪክ ድርጅቶች፤ መንግሥት ለሚወስደው ሕጋዊ እርምጃና በዓባይ ጉዳይ ላይ እየወሰደ ላለው ቆራጥና ትክክለኛ አቋም እስከአሁን ድረስ እያደረግን ያለውን ተካፍሎ ለማጠናክር ዝግጁ መሆናችንን በድጋሜ እንግልጻለን።” ይላል የኢትዮጵያውኑ ማህበረሰብ መግለጫ፡፡

“የኢትዮጵያ ህዝብ የተለመደ አስተዋይነቱና ሚዛናዊነቱን ጠብቆ አንድነቱን ከጽንፈኞች ከጋራ ጠላቶቹ እንዲጠብቅ የተፈናቀሉ ወገኖች የመልሶ መቋቋም ድጋፍ እንዲያኙም” መግለጫው ይጠይቃል፡፡”

በውጭ አገር ተቀምጠው ግጭት የሚቀሰቅሱ መልክቶችን በማኅበራዊ ሚድያ የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ከመንግሥት ጋር በመተባበር በውጭ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለምንኖርባቸው የየሀገራቱ መንግስታት በማስገንዘብና በማጋለጥ ይህን እኩይ እንቅስቃሴ ለመግታትና ለማስቆም አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን። በማለት

መንግሥት ወንጀለኞችን ለፍትኅ ለማቅረብና የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሰብዓዊ መብት ጥሠት፤ ለፖለቲካ ወገንተኝነትና ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ፤ ተፈጥሮ የነበረውን የፖለቲካና ሲቪክ ተሳትፎ ምኅዳር እንዳያጠበው ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን። ብሏል፡፡ በመግለጫው ዙሪያ ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ኢንጂነር ሕዝቄል እስክንድርን የአሜሪካ ድምጽ አነጋግሯል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

ኢትዮጵያውያን ማህበረሰባዊ ድርጅቶች ኔትዎርክ መግለጫ አወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00


XS
SM
MD
LG