በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጠቅላይ ጽ/ቤት መግለጫ


የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብፁዕ ካርዲናል ሊቀ-ጳጳስ ብርሀነ የሱስ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብፁዕ ካርዲናል ሊቀ-ጳጳስ ብርሀነ የሱስ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብፁዕ ካርዲናል ሊቀ-ጳጳስ ብርሀነ የሱስና የመርዋቸው መልእክተኞች ኤርትራ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የቤተክርስትያንዋ ሴክረታርያት አርረጋግጧል።

ካርዲናሉና ቡድናቸው የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስተያን ባደረገችላቸው ጥሪ መሰረት ባለፈው ቅዳሜ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንዳነበር ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች አውሮፕላን ማረፍያ ላይ እንዳስቆሟቸው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ዛሬ ያወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ካርዲናሉንና ቡድናቸውን የጋበዛቸው የኤርትራ ኪዳነ-ምህረት ቤተክርስትያን የተመሰረተችበትን 50ኛ አመት ኢየብልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ እንዳነበር መግለጫው ገልጿል።

ካርዲናሉና ቡድናቸው ከ16 ሰዓታት በላይ በአውሮፕላን ማረፍያው ውስጥ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ በነገታው እሁድ ከሰዓት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ተገደዋል ይላል መግለጫው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አሰና የተባለው የኤርትራ ተቃዋሚ ሳተላይት ቴሌቪዥን ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ-የሱስ የካቲት 16, 2012 አም በአዲስ አበባ ቀባና ካቶሊካዊት ኪዳነ-ምህረት ዓመታዊ ክብረ-በዓል ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ተፈጠረ የተባለው ሰላም ሃሰት ማሆኑንን አረጋግጠን መጥተናል ብለዋል በሚል ያስተላለፈው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል መግለጫው።

የአሰና ቴሌቪዥን ጣብያ ያስተላለፈውን የተሳሳተ ዘገባ እንዲያስተካክልና ማስተባበያ እንዲሰጥ እናሳስባለን ይላል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ዛሬ ያወጣው መግለጫ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG