ዋሽንግተን ዲሲ —
አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ተጠቅመዋል በሚል በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማኅበር የጸረ አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ኤጀንሲ አማካኝነት ምርመራ ከተጀመረባቸው ስድስት አትሌቶች ውስጥ ሁለቱ ቅመሞቹን በትክክል መጠቀማቸው በመረጋገጡ ቅጣት እንደተጣለባባቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ።
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንዲህ ያለውን ነገር አድርገው ቢገኙ እንኳን ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተታለው እና ባለማወቅ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ይላል።
ጽዮን ግርማ ፌደሬሽኑንና አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።