በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ማኅበር "ህወሃትን ትደግፋለች" ሲል ዩናይትድ ስቴትስን ከሰሰ


አንድ የትውልደ ኢትዮጵያዊያን ማኅበር "ህወሃትን ትደግፋለች" ሲል ዩናይትድ ስቴትስን ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:31 0:00

አንድ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ማኅበር "ህወሃትን ትደግፋለች" ሲል ዩናይትድ ስቴትስን ከሰሰ

"ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ህወሃትን በመደገፍ በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እያደረገ ነው" ሲል የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዕድገት ምክር ቤት የተባለው ድርጅት ከሰሰ።

"በአሸባሪነት የተፈረጀውን ቡድን ወደ ሥልጣን ለመመለስ በታለመ ጥረት በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች መጣልን ጨምሮ መንግሥቱን የሚያዳክም መጠነ ሰፊ ግፊት እያደረገ ነው" ሲልም ወንጅሏል።

በሌላ በኩል በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ባለው ቀውስ ላይ ያተኮረ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት የሃገራቸውን አቋም አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ "በኢትዮጵያው ግጭት ህወሃትን ትደግፋለ" በሚል በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚቀርበውን ትችት ውድቅ አድርገዋል።

ከኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዕድገት ምክር ቤት መስራች እና ተባባሪ ሊቀመንበር አቶ ነብዩ አስፋው በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያቀረቧቸውን ክሶች አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እና አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በመንግሥታቱ ድርጅት መድረክ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ተናገሩትን ጨምሮ አቶ ነብዩ አስፋውን ያነጋገረው አሉላ ከበደ ሙሉ ዝግጅቱን እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

XS
SM
MD
LG