በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታስረው የተለቀቁት የሚኔሶታው ባለሀብት ተሺታ ቱፋ ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል


ተሺታ ቱፋ. (Photo: Abdi Mohamud for VOA)
ተሺታ ቱፋ. (Photo: Abdi Mohamud for VOA)

በፈረንጆች ገና ዋዜማ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ታስረው የተለቀቁት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ የትልቅ ኩባኒያ ባለቤት አቶ ተሺታ ቱፋ ትናንት ማክሰኞ ወደመኖሪያቸው ወደ ሚኔሶታ ክፍለ ግዛት ተመልሰዋል።

አቶ ተሺታን በሚኒያፖሊስ ሴንት ፖል አውሮፕላን ጣቢያ ቤተሰቦቻቸው እና የማኅበረሰባቸው አባላት ተቀብለዋቸዋል።

ዛሬ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የሜትሮፖሊታን ትራንስፖርቴሽን ኔትወርክ ኩባኒያ ባለቤት አቶ ተሺታ በደህና መግባታቸውን ገልጸው ስለጉዳዩ በዝርዝር ለመናገር ግን ለጊዜው ዝግጁ እንዳልሆኑ ጠቅሰዋል።

የሚኒሶታ ባለሥልጣናት አቶ ተሽታ ከእስር ተለቅቀው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ይረዱ ዘንድ ቤተሰቦቻቸው መጠየቃቸው ሲታወስ የሚኔሶታ ሴኔተር ኤሚ ክሎቡቻር በትዊተር ባወጡት ጽሁፍ ጽህፈት ቤታቸው ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለልስጣናት ጋር ሲነጋገርበት እንደነበር ጠቅሰው "ተለልቀው ወደቤታቸው መመለስ ላይ የመሆናቸው ዜና እፎይታ ሰጥቶኛል" ብለዋል።

ስለአቶ ተሺታ እስር ጉዳይ ቪኦኤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

እአአ በ1992 በፖለቲካ ስደተኝነት ወደ አሜሪካ የመጡት አቶ ተሽታ ቱፋ ከዕቃ ማጠብ ስራ ተነስተው ብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅሰው እና በመቶዎች የተቆጠሩ ሰራተኞች ያሉት የትራንስፖርት ኩባኒያ ለማቋቋም የበቁ ሰው ናቸው።

XS
SM
MD
LG