No media source currently available
በቻይና ውሃን ግዛት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ለ2 ወራት የሚቆይ የ200 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለ300 ተማሪዎች ለማድረግ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡ በአንጻሩ በውሃን የሚገኙ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከገንዘብ ድጋፉ ይልቅ ተማሪዎቹ ወደ አገር ተመልሰው በማቆያ ቢገቡ እና ከሕብረተሰቡ ጋር ቢቀላቀሉ ሲሉ ለውጭ ጉዳይ እና ለጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት አመልክተዋል፡፡