በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከአብራሪ እስከጠቅላላ መሰናዶው በሴት ባለሙያዎች የተክነናወነ ታሪካዊ በረራ ወደ ባንኮክ


ከየኢትዮጲያ የአየር መንገድ ዌብሳይት የተገኘ ፎቶ
ከየኢትዮጲያ የአየር መንገድ ዌብሳይት የተገኘ ፎቶ

የኢትዮጳያ አየር መንገድ ከብችኛዋ ሙሉ የበረራ ካፒቲይኑ አንስቶ ለበረራው ኣስፈላጊዎቹ ስራዎች በሙሉ በሴቶች የሚክነናወን ጉዞ ምሽቱን ከኣዲስ ኣበባ ወደ ባንኮክ ያመራል።

የኢትዮጳያ ኣየር መንገድ የተመሰረተበትን ሰባኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር በሚያደርገው መሰናዶ ለዛሬ ለየት ያለ ዝግጅት ላይ ነው።

በአውሮፕላን ጣቢያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ መሰናዶው በሴቶች ባለሙያዎች ተከናውኖ በብችኛዋ ሴት ሙሉ የበረራ ካፒቴን አምሳለ ጉዋሉ የሚነዳው ኣውሮፕላን ምሽቱን ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ ይጉዋዛል።

የአየር መንገዳችንን የሰባ ዓመት ክንዋኔ የሴቶች ባለሙያዎቹን ዕድገት በማንጸባረቅ መልካም አጋጣሚ ሆኖ ኣግኝተነዋል ብለዋል የማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዚደንትዋ ወይዘሮ ራሄል አሰፋ። ለምሽቱ ሴቶችና ቤተሰብ ፕሮግራም ቆንጂት ታዬ ጋብዛቸዋለች። ውይይቱን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG