በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሞተር ብልሽት ምክንያት ደብሊን አረፈ


የኢትዮጵያ ኣየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን
የኢትዮጵያ ኣየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን

ከኣዲስ አበባ ተነስቶ በአየርላንድ በኩል ወደ አሜሪካ በመብረር ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በሞተሩ ላይ በተፈጠረ እክል ምክንያት ተመልሶ ወደ ደብሊን ለማረፍ መገደዱ ተገለጸ።

ከአዲስ ኣበባ ተነስቶ በአየርላንድ በኩል ወደ አሜሪካ በመብረር ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በሞተሩ ላይ በተፈጠረ እክል ምክንያት ተመልሶ ወደ ደብሊን ለማረፍ መገደዱ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ዛሬ ማለዳ ከአየርላንድ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ዋሽንግተን ጉዞ በማድረግ ላይ እንዳለ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ችግር ስላጋጠመው ነው ወደ ደብሊን የተመለሰው።

የበረራ ቁጥሩ ET-ARF የሆነው 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን አንደኛው ሞተር ስራ በማቆሙ ምክንያት በደብሊን ለማረፍ ተገዱዋል ብሉዋል።

አሜሪካ ዋሽንግተን መዳረሻው የነበረው ቦይንግ አውሮፕላን 300 መንገደኞችን አሳፍሮ እንደነበርም አይሪሽ ሚረር ዘግቧል።

አውሮፕላኑ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ማረፉም ተመልክቷል።

የዚህ አውሮፕላን ችግር እስኪስተካከልም ተሳፋሪዎቹን ወደ አሜሪካ የሚያደርስ ሌላ አውሮፕላን ከጀርመን ፍራንክፈርት ወደ ደብሊን መላኩም ነው የተነገረው።

ለአውሮፕላኑ ወደ ደብሊን መመለስ የግራ ሞተሩ ስራ ማቆም በምክንያትነት ቢጠቀስም በአጠቃላይ የተፈጠረው ችግር መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።

አየር መንገዱ በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር መንገደኞቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፥ አውሮፕላኑ በሰላም እንዲያርፍ ለተባበሩ የአየር መንገድ ሰራተኞች ምስጋና አቅርቧል።

ሙሉውን ዝርዝር ከተያያዘው ይድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሞተር ብልሽት ምክንያት ደብሊን አረፈ /ርዝመት -1ደ36ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:35 0:00

XS
SM
MD
LG