በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም

የበረራ ቁጥሩ ኢቲ-302 የሆነውና ከ15 ቀን በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስዔ ገና እየተጣራ በመሆኑ፣ የተሟላ መልስ እስከሚገኝ በሚደረገው ጥረት ያልተቆጠበ ትብብር እንደሚያደርጉ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገበረማርያም አስታወቁ።

አቶ ተወልደ ዛሬ ሰኞ ይፋ ባደረጉት መግለጫ፣ የተሟላ መልስ ከመገኘቱ አስቀድሞ፣ የአንድም ሰው ሕይወት ቢሆን አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድረግ ተገቢ አይደለም» ብለዋል።

አደጋው ከኢንዶኔዥያው ላይን ኤር ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ከግምት በማስገባት፣ ያሉንን MAX 8 አሮፕላኖች በሙሉ እንዳይበሩ አድርገናል» ያሉት አቶ ተወልደ፣ ይኸው አውሮፕላን በመላው ዓለም እንዳይበር መደረጉንም አክለው አስታውሰዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች የአብራሪዎቹን ብቃት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ዘገባ ቢያወጡም፣ «አብራሪዎቹ የተሟላና ተገቢው የሲሙሌተር ሥልጠና ያላቸው እንደነበሩም አቶ ተወልደው አክለው ገልጸዋል። «ይህ አሳዛኝ አደጋ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በትክክል የሚገልጸው አይደለም» ብለዋል ዋናው ሥራ-አስፈጻሚው።

በተያያዘ ዜና፣ ዋና ቢሮው ኒው-ዮርክ የሆነውን 'The New York Times' ጋዜጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚከስ አቶ ተወልደ አስታወቁ።

ጋዜጣው ይፋ ባደረገው አንድ ዘገባ፣ የወደቀው የቦይንግ 737 max 8 አውሮፕላን አብራሪ፣ በዚያ አውሮፕላን ላይ ተገቢውን ሥልጠና አልወሰደም» ብሎ መጻፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊመሰርት ያቀደው ክስም በዚህ ዘገባ መነሻነት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ተወልደ፣

«ዋሽንግተን ፖስትም፣ ይህንኑ መሰረተ-ቢስ የሀሰት ዜና ዘግቧል» ብለዋል። አክለውም፣ «በእነዚህ መገናኛ አውታሮች ላይ አስፈላጊ የሆነውን ህጋዊ እርምጃ ሁሉ እንወስዳለን» ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG