በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ደመና አሜሪካ ሲደርስ ሃሪኬን ይሆናል


"የኢትዮጵያ የአየር ሁኔታ በአሜሪካ ላይ ከባድ ተፅዕኖ አለው"

በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ደመናዎች ሰሃራ በረሃንና አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው አሜሪካን በከባዶቹ የባሕር ማዕበሎች (ሃሪኬኖች) እንደሚመቷት አንድ ባለሙያ አስታወቁ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የከኔክቲከት ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰርና የአየርና የውኃ የተፈጥሮ ሃብቶች ተመራማሪው ዶ/ር መኮንን ገብረሚካኤል ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ የአየር ንብረት ለውጥ በተለይ ለድኆቹ ሃገሮች እጅግ የከበደ መዘዝ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ይህም ጫና የሚንፀባረቀው በሰዉ ጤና፣ በግብርናው ዘርፍ፣ ኃይል በማመንጨት ችሎታና አቅም እንዲሁም በውኃና በሌሎችም ሃብቶች ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ዓለም ባለፈው ታሕሣስ 2002 ዓ.ም ዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሃገን ላይ ተደርጎ ከነበረው የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ብዙ ውጤት በጉጉት ጠብቆ እንደነበና የተገኘው ግን ትንሽ በመሆኑ ዓለም ተስፋ ቆርጦና አዝኖ መበተኑን አስታውሰዋል፡፡

ሰሞኑን በሜክሲኮዋ ከተማ ካንኩን የተካሄደው ጉባዔ ምንም እንኳን በኮፐንሃገን ተስፋ መቁረጥ ምክንያት ቀዝቃዛ አቀባበል የተደረገለት ቢሆንም በውጤቱ ግን ካለፈው ጉባዔ የተሻለ መሆኑን፣ በገንዘብም ይሁን ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመቆጣጠር በኩል ተጨባጭ እንቅስቃሴ የታየበትና ዓለም በትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዘ መሆኑን የሚያሣይ እንደነበር ዶ/ር መኮንን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም የካርቦን ልቀትን ለመቆጣጠር ሃገሮች የተስማሙበት የኪዮቶ ፕሮቶኮል ኃይሉን ሊያጣ የቀረው አንድ ዓመት ብቻ የመሆኑ ጉዳይ እንቅስቃሴው ይበልጥ የተፋጠነ እንዲሆን የሚያሣስብ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ ቃለምልልሱን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG