አዲስ አበባ —
በበጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን የተጀመረው “የበጎ ሰው ሽልማት” ሥነ-ሥርዓት ዘንድሮም ለሦስተኛ ዓመት ተካሄዷል።
አምና በሰባት ዘርፎች የተሰጠው ሽልማት ዘንድሮ ወደ አሥር ከፍ ብሎ በሣይንስና በኪነጥበብ፣ በበጎ አድራጎት፣ በሠላም፣ በንግድና ሥራ ፈጠራ፣ በስፖርት፣ በማኅበራዊ አገልግሎት፣ በጥናት፣ በመገናኛ ብዙኃንና ጋዜጠኝነት እንዲሁም በቅርስና ባህል የጎላ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ኢትዮጵያዊያን ተሰጥቷል።
የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን ተከታትሎ እስክንድር ፍሬው የላከውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።