በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በአዲስ አበባ የዓለም ሊበራል ፓርቲዎችን ጉባዔ ሊያሰናግድ ነው


ከሦስት ዓመታት ተከታታይ ውይይት በኋላ ኢዴፓ የሊብራል ፓርቲዎች ግንኙነት አውታር አባል መሆኑን አስታወቀ።

የኢዴፓ አመራር አባላት በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ በጠሩት ጋዜጣዊ ጉባዔ በዓለምአቀፍ ሊበራል ፓርቲዎች አውታር አባልነታቸው ምክንያት የምሥራቅ አፍሪቃ ሊበራል ፓርቲዎችን ጉባዔ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲያዘጋጅ ፓርቲአቸው መመረጡን ገልፀዋል።

ኢዴፓ የሊበራል ፓርቲዎች ግንኙነት አውታር ለመሆን የበቃው የኢዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና ድጋፍ ሰጭው፤ የባሕር ማዶ የዴሞክራሲ ተቋማትን የሚያበረታታውና የሚያግዘው ዌስትሚንስተር ፋውንዴሽን ፎር ዴሞክራሲ ኢን አፍሪካ - Westminster Foundation for Democracy የሚባለው መሠረቱ እንግሊዝ የሆነው ድርጅትና የአፍሪቃ ሊበራል ፓርቲዎች ዋና ማዕከል ፓርቲውን ተቀብለው የግንኙነቱ አውታር አባል እንዲያደርጉ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ ባደረጉት ጥረት መሆኑን ሊቀመንበሩ አቶ ሙሼ ሰሙ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በሚደረገው ጉባኤ ላይ ከሚገኙት አንዳንዶቹ ገዥ ፓርቲ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የእንግሊዙ ሊበራል ዴሞክራቲክ ሙቭመንት፣ የሲሼልስ፣ የኬንያና የሴኔጋል ሊበራል ዴሞክራት ፓርቲዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG