ኢትዮጵያ፣ ከዐሥር ዓመት በኋላ፣ ከዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ልትጠብቅ እንደማይገባ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ተናገሩ፡፡ፕሬዚዳንቱ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ጋራ፣ ዛሬ ባደረጉት ውይይት፣ አገሪቱ፥ የቀጣይ ዐሥር ዓመታት ዕቅድ አዘጋጅታ ልትሠራ እንደሚገባ የገለጹት ባንጋ፣ ለዚኽም ተግባራዊነት፣ የገንዘብ እና የዕውቀት ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
ባንጋ፣ በዛሬው ዕለት፣ በዓለም ባንክ ከሚደገፍ ፕሮጀክት ጋራ ትስስር ካላቸው ሥራ ፈጣሪ ሴቶች ጋራ ተገናኝተውም ተነጋግረዋል፡፡ የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን ጥረት ያደነቁት ፕሬዚዳንቱ፣ ይበልጥ ስኬታማ እንዲኾኑ፣ የተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ፣ የሦስት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸውን ዛሬ አጠናቀዋል፡፡
ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም