በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ጤና መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ነው" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም


የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም

አዲሱ ተመራጭ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የጤና ጥበቃ ሥራቸው ለሁሉም ሰው የሚዳረስ የሰብዓዊ መብት እንዲሆን የመሥራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።

አዲሱ ተመራጭ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የጤና ጥበቃ ሥራቸው ለሁሉም ሰው የሚዳረስ የሰብዓዊ መብት እንዲሆን የመሥራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሀምሌ ወር ሥራ ሲጀምሩ የዓለም የጤና ድርጅትን በመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ።

በዚህ ምርጫ ከሁለት ሌሎች ዕጩዎች የጠበቀ ፉክክር ቢገጥማቸውም በስተምጨረሻ ከ185 የዓለም የጤና ድርጅት አባል ሀገሮች የ133ቱን ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፉት።

"ጤና መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ነው" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

ዶ/ር ቴድሮስ ያገኙት ሰፊ ድጋፍ የዓለም የጤና ድርጅትን ራዕይ ለመተግበር የመተማመኛ ድምፅ ይሆነኛል ብለዋል። በሥራቸውም ጤና መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት መሆኑን በተግባር ማሳየት እንደሚሆን አብራርተዋል።

“ግማሽ የሚሆነው ማህበረሰባችን የጤና አገልግሎቶች አያገኝም። አጠቃላይ የሆነ የጤና ጥበቃ መሰረታዊ መብት ነው። በስተመጨረሻ ደግሞ ጤና የማኅበረሰብ ልማትና ብልፅግናን ያመጣል። ስለዚህ የእንቅስቃሴያችን ዓብይ ትኩረት፤ የጤና አገልግሎቶችን ለሁሉም ማዳረስ ነው” ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ።

"ጤና መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ነው" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG