በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ


ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል" ሲል ተናግሯል።

ኢትዮጵያ የስንዴ ምርቷ ስላደገ "ስንዴ ከውጭ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቷል" ብላለች።።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የውጭ ሀገር የስንዴ ምርት ታስገባ ነበር። መግለጫው አያይዞም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠ በ2022/23 የምርት ዘመን ኢትዮጵያ 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ የስንዴ ምርቱ መጠን በቀጠለው ዓመት ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን አውስቷል።

አያይዞም ሀገሪቱ በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏ ስንዴ ከውጭ መግባቱ ይቆማል ማለት ግን እንዳልሆነ ያሳሰበው መግለጫው በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት አሁንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥቱ መግለጫ የወጣው ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ወራት ያህል የውጭ ርዳታን እንዲቆም ባደረገችበት በአሁኑ ወቅት ቢሆንም የአሜሪካ የውጭ ርዳታ ስለመቆሙ አላነሳም።

የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች የአጣዳፊ ጊዜ ድጋፎች ከዕቀባው ውጪ እንዲሆኑ ትዕዛዝ መተላለፉን ግልጽ አድርገዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሕይወት አድን መርሐ ግብሮች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሚያስችል “ጥቅል መሳሰቢያ” መስጠታቸውን ገልጸዋል።

“ምግብ ፣ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ሕይወት አድን የሆነ አጣዳፊ አገልግሎት በዕቀባው አይካተትም " ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG