በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ የዳሮ ለቡ የዛሬ ውሎ


ምዕራብ ሐረርጌ ዞን
ምዕራብ ሐረርጌ ዞን

ምዕራብ ሃረርጌ ዳሮ ለቡ ወረዳ ውሰጥ ዛሬ ተጣለ ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በገለፁት ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ፣ አንድ ሰው መቁሰሉና ሰባ ግመሎች መዘረፋቸው ተገለፀ። የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ግን ዛሬ ተፈጠረ የተባለውን ሁኔታ አስተባብለዋል።

ምዕራብ ሃረርጌ ዳሮ ለቡ ወረዳ ውሰጥ ዛሬ ተጣለ ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በገለፁት ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ፣ አንድ ሰው መቁሰሉና ሰባ ግመሎች መዘረፋቸው ተገለፀ።

የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ግን ዛሬ ተፈጠረ የተባለውን ሁኔታ አስተባብለዋል።

ዳሮ ለቡ ወረዳ ውስጥ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ጎሣዎችና ብሔረሰቦች አባላት በመቶዎች ዓመታት ለሚቆጠር ጊዜ አብረው መኖራቸውን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ በዚህች የሶማሌ ብሄረሰብ አባላት በዝተው በሚኖሩባት የኦሮምያ ክልል ውስጥ በምትገኝ “ሰርጥ” ልትባል በምትችል አካባቢ ባለፉት አምስት ወራት የነበረው ሁኔታ የከፋ ነው የሚመስለው። በርግጥ ምዕራብ ሃረርጌ ውስጥ ባሉ አምስት የኦሮምያ ወረዳዎች ውስጥ ሁኔታውን ለማርገብና በነዋሪዎቿ መካከል መግባባትና ፍቅርን ለመመለስ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸው እየተሰማ ነው። ሰዉም የሚፈልገው ይህንኑ ነው።

ለዝርዝሩ የአካባቢውን ነዋሪና የዞኑን የመንግሥት ቃል አቀባይ ሃሣቦች የተንፀባረቁበትን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኦሮምያ የዳሮ ለቡ የዛሬ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG