በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ መርማሪዎች ቡድን የሰላም ጥረቱን ያጨናግፋል ስትል ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች


ፎቶ ፋይል፦ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ወቅት ደብረታቦር፣ ኢትዮጵያ፣ እአአ 11/2021
ፎቶ ፋይል፦ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ወቅት ደብረታቦር፣ ኢትዮጵያ፣ እአአ 11/2021

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር መነሳቱ ባለፈው ጥቅምት ከተፈረመው የሰላም ሥምምነት ወዲህ የታዩ መሻሻሎችን ያስተጓጉላል ስትል ኢትዮጵያ አስጠንቅቃለች፡፡

“በተመድ ለኢትዮጵያ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን በአፍሪካ ኅብረት የተመራውን የሠላም ሂደትና በፕሪቶሪያ የተፈጸመውን የሠላም ሥምምነት በመርዛማ ትርክት የሚበክል ነው” ሲሉ የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአገሪቱ ተቋማት እየተደረገ ያለውን ጥረትም ያዳክማል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ ኅብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ መናገራቸውን ኤኤፍፒ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ትዊተር ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ባለፈው መስከረም ባወጣው የመጀመሪያ ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመፈጸማቸው ማስረጃ እንዳገኘ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚሽኑን ሪፖርት ውድቅ አድርጓል፡፡

ሶስት ዓባላት ያሉት የተመድ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኤርትራ እና ህወሓት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲመረምሩና ጥሰት ፈጻሚዎቹንም ለፍርድ እንዲያቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG