የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች፣ በማኅበረሰብ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በማቃለል ኹለንተናዊ ለውጥን ለማምጣት ኹነኛ ሚና አላቸው፡፡ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ቀውሶች በሚፈራረቁባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ ሀገራት ደግሞ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
በኢትዮጵያ፣ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በጦርነትም ኾነ በሌሎች ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የተጎዱ እና ተጋላጭ የኾኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የመደገፍ ሥራ ከሚያከናውኑ ድርጅቶች ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ፈጣን ደራሽነት የሚሹ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች፣ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እየታዩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ በተለይ ወጣቶች ቀዳሚ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ይታመናል፡፡ ለመኾኑ፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎ እንዴት ይገለጻል?
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የዐዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ሥር የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን እያበረከቱ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አራት ወጣቶች ስለተሳትፏቸው አውግተውናል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም