በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ትላንት ጠዋት በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥና አንድ ፖሊስ መገደላቸውን የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበበ ወርቁ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ሁለት ሌሎች ሰዎችም በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን ተናግረዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች ግድያውን መፈፀማቸውን አምነዋል። “ሰዎቹን አግተን ሳይኾን ማርከን ወስደናቸዋል” ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም