በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አወጣ

ኢትዮጵያ ውስጥ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎችና በተለያዩ ቦታዎች ግጮቶች እንደሚካሄዱ የሚሰማው ወሬ በተለይም ብሄር ተኮር መሆናቸው እጅግ ያሳስባል። ይህም በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮምያ ክልል መካከል የተካሄዱትን ብዙ ሞትና ውድመት ያስከተሉትን ግጭቶች ያካትታል ይላል - የአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት ቃል አቀባይ ያወጣው መግለጫ። የአውሮፓ ሕብረት ለሰለብዎቹ ቤተሰቦች ሃዘኑን ገልጿል፡፡

በሁሉም ዓይነት ግጭቶች ነፃ ምርመራ እንዲካሄድ ያስፈልጋል። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጉዳዩን የሚመረምር ግብር ኃይል መመስረታቸው መልካም ነው፣ ክልላዊና ፌደራላዊ የፖሊስ ኃይሎች የሁሉም ዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅ መቆጠብ ይኖርባቸዋል - ሲልም መግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በሕገ መንግሥቱ የሰፈረው የግጭት አፈታት ዘዴ በፍጥነት እንዲተገበር ያስፈልጋል። ሕዝቡ የሚያቀርበው እሮሮ በሰላማዊ መንገድና ገንቢ በሆነ አያዝ መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው ከባለድርሻዎች ጋር አካታች የሆነ ፖለቲካዊ ንግግር በማድረግ ብቻ ነው፣ ሲል የአውሮፓው የውጭ ጉዳይ አገልግሎት መግለጫ መክሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG