በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ቢያንስ የአንድ መቶ ሃምሳ ሰው ህይወት ማለፉ ተገለጠ


በኢትዮጵያ ዝነኛው የአሮምኛ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተቀሰቀሱ ሁከቶች በተያያዘ ቢያንስ አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በፖለቲካዊ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በሀገሪቱ ውጥረቱ አይሏል፥ በተወለደበት የኦሮሚያ ክልልም የተቃውሞ እንቅስቃሴው ተቀጣጥሏል

ባለፈው ሳምንት ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች ወይም ብሄረሰብ ተኮር በሆኑ ግጭቶች ከተገደሉት መካከል የሚበዙት በኦሮሚያ ክልል ሲሆኑ አዲስ አበባ ውስጥም የተገደሉ እንዳሉ ተገልጿል

ቁጥራቸው ቢያንስ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸውም ተመልክቷል

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት አገልግሎት ያቋረጠ በመሆኑ ለመብት ድርጅቶች የግድያዎቹን ጉዳይ ለመከታተል አዳጋች እንደሆነባቸው ዜናው ጨምሮ አውስቷል

XS
SM
MD
LG