በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አንድ ዓመት ሞላው


ፎቶ ፋይል፡ በታኅሣሥ ወር መግቢያ (Dec. 17, 2015)በኦሮሚያ ክልል በሆለን ኮሚ ከተማ ዲንካ ጫላ የተባለ መምሕር በታጣቂዎች መገደሉን በቀብሩ እለት ቤተሰቦቹ ይናገራሉ
ፎቶ ፋይል፡ በታኅሣሥ ወር መግቢያ (Dec. 17, 2015)በኦሮሚያ ክልል በሆለን ኮሚ ከተማ ዲንካ ጫላ የተባለ መምሕር በታጣቂዎች መገደሉን በቀብሩ እለት ቤተሰቦቹ ይናገራሉ

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? የአሜሪካ ድምጿ ማርታ ቫንዶርፍ ከብራስልስ ባጠናቀረችው ዘገባዋ ታነሳዋለች።

በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? በዚህ ዘገባ ተካቷል።

በሌላ በኩል የኦሎምፒክ የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ፣ የግንቦት ሰባቱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዶ/ር መረራ ጉዲና በብራስልስ አውሮፓ ሕብረት ጽ/ቤት ተገኝተው ለኅብረቱ የፓርላማው አባላት በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ነው ያሉትን የመብት ጥሰትም አብራርተዋል።

ዝርዝሩን በድምፅ ለማድመጥ

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አንድ ዓመት ሞላው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00

በኢትዮጵያ ባለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ የኦሎምፒክ ሯጩ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ስሞ ጎልቶ ይነሳል። በዘንድው የሬዮ ኦሎምፒክ ላይ የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በውድድሩ ማጠናቀቂያ ላይ እጆቹን ወደ ላይ በማጣመር በኢትዮጵያ ፤የኢትዮጵያን መንግሥት ለመቃወም መለያ የሆነን ምልክት በማሳየቱም የዓለምን ትኩረት ስቧል።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ይህ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት አንደኛ ዓመት በትናንትናው ዕለት በብራስልስ አውሮፓ ሕብረት ጽ/ቤት ተገኝቶ በኢትዮጵያ አሁን ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ አደገኛ ችግር ይፈጠራል የሚል ስጋት እንዳለው ለኅብረቱ የፓርላማ አባላት አስረድቷል።

የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ
የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ

“ይሄ ችግር አሁን ባለበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው፡ ወደፊት ሕዝቡ ላይ ትልቅ አደጋ የሚያስከትል ነው። እስካሁን ብዙ አደጋ ደርሷል። ብዙ ህይወት ጠፍቷል። እኔ አሁን እያደረኩ ያለሁት ከዚህ በፊትም በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተገኝቼ እንዳደረኩት ችግሩን ማሳወቅ ነው። ለምሳሌ አሁን ኢንተርኔት እና ብዙሃን መገናኛ ተዘግቷል። መንግስት ከሚያስተላልፈው መረጃ ውጪ ሕብረተሰቡ ምንም የመገናኛ ብዙሃን የለውም”

ፈይሳ አያይዞም አሁን በኢትዮጵያ የሕዝብ ድምጽ በመታፈኑ ምክንያት በእርሱ በኩል በተቻለው ሁሉ ችግሩን ለዓለም ሕዝብ ለማሰማት እየጣረ መሆኑን ተናግሯል።

ሁለተኛው ተናጋሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ነበሩ። ዶ/ር ብርሃኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ሲሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ድርጅታቸውን በአሸባሪነት ፈርጆ መንግስትን በኃይል በመገልበጥ ክስ ወንጅሎ በሌሉበት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰው ናቸው። ዶ/ር ብርሃኑ ቀጣዩ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ማሳያ ነው የሚል እምነት አላቸው።

በኢትዮጵያ አሁን ያለውን ሁኔታ ለአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አባላት ሲያስረዱም የተፈጠረው ውጥረት ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የከፋ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ግፊት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

“የዚህ አስተዳድር ወዳጆች ያደርጋሉ ብየ ተስፋ የጣልኩት፤ በኢትዮጵያ በሁከት ወደስልጣን ለመምጣት የሚደረግ ጉዞ እንዳከተመለት ሊያስስቡ ይገባል ብየ ነው። አማራጮች መፈለግ አለባቸው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ይሄም አማራጭ ጊዜው ሳይዘገይ በፍጥነት በአደጋ ላይ ያለውን ሁኔታ መሬት ማስያዝን ይጠይቃል።”

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የተቀሰቀሰው ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው ጊኒንጪ ከተማ በሕዳር ወር መግቢያ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዙሪያ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረውን የማስተር ፕላን ንድፍ የኦሮሞ ገበሬዎችን ያፈናቅላል በሚል ነበር ተማሪዎች የተቃወሙት። የዛሬ ዓመት ይህ የቃውሞ ከመቀስቀሱ አስቀደሞ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ተመሳሳይ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር።

በቅርቡ በእሬቻ በዓል ላይ በቢሾፍቱ የነበረው ተቃውሞ
በቅርቡ በእሬቻ በዓል ላይ በቢሾፍቱ የነበረው ተቃውሞ

ከዚህ ቀደሙ ያገረሸውና ልክ የዛሬ ዓመት በጊንጪ የተቀሰቀሰው ተቃዎሞ ወደ ሌሎች ቦታዎች ወዲያውኑ ነበር የተዛመተው። የተቃዋሚዎቹ ጥያቄም መጀመሪያ ባነሱት የመሬት ዝርፊያ ሊቆም ይገባል ጥያቄ ተወስኖ አልቆየመ። ተቃውሞአቸ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በተስፋፋ ቁጥር ጥያቄውም የብሔር የበላይነት ይቁም፣ የፖለቲካ ነፃነት ይከበር ፍትሃዎ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ይኑር የሚሉ ጥያቄዎችንም ጨምሯል።

በዚህ የተቃውሞ ጊዜም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት ናቸው። እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ለስድስት ወር በሚቆይ አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ስር ናት።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀምንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ባለፈው ሳምንት መግስት የካቢኔ አባላቱን እንደገና በማዋቀር የወሰደው ርምጃ አሁንም ከተቃውሞው ጥያቄ ጋር የማይመጣጠን የተራራቀ ምላሽ እንደሆነ ይናገራሉ።

“መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀምጦ በጠረንጴዛ ዙሪያ ለንግግር ራሱን ካላዘጋጅ። ከመግስት ጋርም ተቀምተው ለመነጋገር ደስተኛ የማይሆኑ አካላት በጋራ ሆነው አንድ ሰላማዊ ውይይት መፈጠር እስካልተቻለ ድረስ በዚች ሀገር ላይ ሰላምን ለማምጣት ማሰብ መቼም ቢሆን የማይሳካ ጉዳይ ነው”

በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ
በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ

በሊደን ዩኒቨርስቲ በአፍሪካ ጥናት ማኦአከል ፕሮፌሰር የሆኑት ጃን አቢኪን የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ላይ ብቻ መተማመን የለበትም ይላሉ።

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዚህ ሣምንት የኢትዮጵያን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ “አሁን መንግስት የወሰደው የፀጥታ እርምጃ ተገቢ ምላሽ የሚፈልጉ ጉዳዮችን የሚሸፋፍን ነው። ሌላ ዙር ሁከት ከመቀስቀሱ በፊት መንግስት ሊያስብበት ይገባል ብሏል”

ዝርዝርሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አንድ ዓመት ሞላው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00

XS
SM
MD
LG