በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ከምትሰጠው የልማት ዕርዳታ ትልቁን የምታገኘው ኢትዮጲያ መሆንዋን አስታወቀች።


ኢትዮጲያ ረሃብና ድህነትን ለማጥፋት ላወጣችው ግዙፍ ዕቅድ ለጋሽ መንግሥታት የሚሰጡትን ዕርዳታ በመጨመር ላይ መሆናቸውን ጠቅሶ የአዲስ አበባው የቪኦኤ ዘጋቢ Peter Heinlein ገልጧል።

ብሪታንያ በመጪው አራት ዓመት ውስጥ ለኢትዮጵያ የሁለት ቢሊዮን ዶላር የልማት ዕርዳታ እንደምትሰጥ ያስታወቁት በሀገሪቱ የብሪታኒያ ተራድዖ መርሃ ግብር ኃላፊ Howard Taylor ናቸው።

አገራቸው ለኢትዮጲያ የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ለማሳደግ የተወሰነው የሀገሪቱን የዕርዳታ ፍላጎት መጠንና በቅርብ ዓመታት ያስመዘገበቸውን ዕመርታ መሰረት በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል።

ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG