በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ አምስት የውጭ ቱሪስቶች ተገደሉ


የኤርታ አሌ አካባቢ በካርታ ላይ
የኤርታ አሌ አካባቢ በካርታ ላይ

በኢትዮጵያ የአፋር ክልል አምስት አውሮፓዊያን ሀገር ጎብኚዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

አምስቱ ቱሪስቶች ሰኞ ዕለት የተገደሉትና ሌሎች ሁለት አብረዋቸው የነበሩ የተጠለፉት በክልሉ በጎብኚዎች መስኅብነት በሚታወቀውና ኤርትራና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት አቅራቢያ በሚገኘው በኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተዘግቧል።

“ጥቃቱ የኤርትራ ድርጊት ለመሆኑ ጥርጣሬ የለኝም” ሲሉ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ፕሮሞሽንና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ጌታቸው ረዳ ከስሰዋል፡፡

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ ዓብዶ በሰጡት ምላሽ ክሱን ውድቅ አድርገዋል።

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG