በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ጎብኝዎችን አርቋል ተባለ


በቢሾፍቱ በኢሬቻ በዓል ወቅት/ፎቶ ፋይል/
በቢሾፍቱ በኢሬቻ በዓል ወቅት/ፎቶ ፋይል/

በአለፉት አስርት አመታት በርካታ ጎብኝዎችን በመሳብ፤ “መጎብኘት ከአለባቸው” የዓለም ሀገሮች ተርታ ተሰልፋ የቆየችው ኢትዮጵያ ጭስ አልባ ኢንዱስትሪ ተቀዛቅዟል።

በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ የተፈጸሙ ግድያዎችና በአሳለፍነው ወር የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ጎብኝዎችን አርቋል።

ቤተጊዮርጊስ፤ ላሊበላ
ቤተጊዮርጊስ፤ ላሊበላ

የቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚቀጥራቸው፣ የሚያስተዳድራቸው የንግድ ተቋማትና ግለሰቦችም ገቢያቸው ማሽቆልቆሉን ይናገራሉ።

ኢትዮጵያ ለታሪካዊ ስፍራዎቿ ብቻ ሳይሆን ለመልከዓ ምድሯና በአፍሪካ ሠላምና ጸጥታ የሰፈነባት ሀገር ሆና በመቆየቷ፤ ጎብኝዎች በስፊው ይጎርፉባት ነበር።

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙት የላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቲያኖች በሽህዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎችን በየዓመቱ ይስባሉ።

ከሶስት ሳምንታት በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከወጣ ወዲህ፤ የጎብኞውች ቁጥር ተመናምኗል።

ፋሲል ግንብ
ፋሲል ግንብ

ማርተ ፋን ደር ቮልፍ ከአዲስ አበባ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ሔኖክ ሰማእግዜር ይዞ ቀርቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ጎብኝዎችን አርቋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:52 0:00

XS
SM
MD
LG