ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት ተዘግቶ የነበረውን የኤርትራ ኤምባሲዋን በአዲስ መልክ ከፍታለች።
የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በዘገበው መሰረት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በተደረው አጭር ሥነ ስርዓት ኤምባሲውን ከፈቱ።
የሁለቱም ሀገሮች ግንኙነት የተሻሻለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከ18 ዓመታት በፊት የተፈረመውን ውል እንደምታከብር ባለፈው ሰኔ ወር ካስታወቁ በኋላ ነው። በሁለቱም ሀገሮች መካከል በተካሄደው ጦርነት በ70,000 የሚገመቱ ሰዎች ማለቃቸው የሚታወቅ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ