በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ከአይ ኤም ኤፍና ባንክ ጋር የሚደረገው ድርድር ከተሳካ ኢትዮጵያ 10.5 ቢሊየን ዶላር ታገኛለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ


ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ከዓለም ባንክ ጋር ለረጅም ጊዜ እየተካሄደ ያለው ድርድር ከተሳካ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የ10.5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ልታገኝ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ።

በከፍተኛ የህዝብ ብዛቷ የምትታወቀው፣ ከከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና ለረጅም ግዜ ከዘለቀ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር የምትታገለው ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ዕዳቸውን መክፈል ካልቻሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ሦስተኛዋ ሆናለች።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ጋር እያካሄደች ባለው የማሻሻያ ፕሮግራም ስር 3.5 ቢሊየን ዶላር ለመበደር ስትጥር ቆይታለች። አንድ የምዕራብ ሀገር ዲፕሎማትም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ3.5 ቢሊየን ዶላር የበጀት ድጋፍ እና ሌላ 3.5 ቢሊየን ዶላር በዕዳ ሽግሽግ ለማግኘት እየሞከረች እንደነበር ተናግረዋል።

የተለያዩ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያ ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ከአይኤምኤፍ ለማግኘት፣ በ50 ከመቶ ከጥቁር ገበያው ተመን በታች እየተሸጠ ያለውን የመገበያያ ብሯን ለማዳከም መስማማት ይኖርባታል።

አሁን ግን በአንዳንድ ወዳጅ ሀገሮች ድጋፍ ብዙዎቹ ሀሳቦቻችን ተቀባይነት ያገኙ ይመስላል"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ባደረጉት ንግግር፣ "ከአይኤምኤፍ እና ከዓለም ባንክ ጋር ሰፊ ንግግር፣ ድርድር እና ውይይት ስናደርግ ቆይተናል። እኛም ጠንከር ያለ አቋም ስላለን እና እነሱም በኛ ላይ ጠንከር ያሉ ስለነበሩ ንግግሩ አምስት አመት ፈጅቷል" ብለዋል።

"አሁን ግን በአንዳንድ ወዳጅ ሀገሮች ድጋፍ ብዙዎቹ ሀሳቦቻችን ተቀባይነት ያገኙ ይመስላል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ከተሳካ እና በማሻሻያዎቹ ላይ ከተስማማን ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አመታት 10.5 ቢሊየን ዶላር ታገኛለች" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው መንግስት ወዲያውኑ ተግባራዊ ሊያደርጋቸው ፈቃደኛ ያልሆኑባቸው ማሻሻያዎች እንዳሉ ያለተጨማሪ ማብራሪያ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር "አሁን መስተካከል አለባቸው ብለን የምናስባቸው እና ባሉበት ሁኔታ መቆየት አለባቸው ብለን የምናስባቸው ጉዳዮች አሉ" ያሉ ሲሆን "እነዚህ ምክረ ሃሳቦች ተቀባይነት ካገኙ እና ስምምነት ላይ ከደረስን፣ ከፊት ለፊታችን ዕድል ይጠብቀናል። ይህ የማሻሻያ አጀንዳ የዕዳ ጫናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG