በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት መግለጫ


Tigray Region
Tigray Region

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በአሜሪካ ድምጽ ላይ ቀርበው ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት የቅማንት ተዋጊዎችን አስታጥቀዋል ማለታቸውን ተቃወመ።

ህወሃት የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን አስታጥቋል መባሉ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግፋቸውን ለመሸፈን ሶስተኛ ወገን ላይ ጣታቸውን ለመጠቆም ያደረጉት ነው ብሎታል።

በዚሁ "የሶስተኛ ወገን ልክፍት፥ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ" በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ህወሃት በምዕራብ ኢትዮጵያ ወለጋ ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሥትን ይወጋል መባሉንም በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ ሰራዊት ሊኖረው አይችልም፤ ክሱ ይሉኝታ የጎደለው የሚዲያ ልፈፋ ነው ሲል አጣጥሎታል፤

የኦሮምያ ክልል ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ህወሃት ከአማጺ ቡድን ጋር ታጥቆ እየተዋጋ ነው ሲል መወንጀሉ ይታወሳል፥

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት መግለጫ በመቀጠል ሰሞኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኦሮምያ እና በአማራ ክልሎች የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙ ጠቅሶ ያወጣውን ሪፖርት "ጸሃይ የሞቀው ዕውነታ" ካለ በኋላ የሁለቱ ክልሎች ባለሥልጣናት ሪፖርቱን ማስተባበላቸውን ኮንኗል።

XS
SM
MD
LG