በኢትዮጵያ፣ ለትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች እና ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ሲሰጥ የቆየው የካሳ መጠን መሻሻሉን፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ዛሬ ኀሙስ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የመድን ፈንድ እና የመንገድ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዲሬክተር አቶ ጀማል አባሶ፣ ከዚኽ ቀደም ሲሰጥ የነበረው የሕይወት ካሳ ክፍያ ከ40ሺሕ ወደ 250ሺሕ ብር ማደጉን ገልጸው፣ ለከባድ የአካል ጉዳት የሚከፈለው የካሳ መጠንም እንዲሁ ከ40ሺሕ ወደ 250ሺሕ ብር ማደጉን ተናግረዋል፡፡
በመግለጫው ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ በርኦ ሐሰንም፣ ዐዲሱ የካሳ ማሻሻያ ደንብ፥ በትራፊክ አደጋ ተጎጅዎች እና በተጎጂ ቤተሰቦች ሲነሣ የቆየውን የፍትሐዊነት ጥያቄ ትርጉም ባለው መልኩ መልሷል ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም