ዋሺንግተን ዲሲ —
“በወታደራዊው የደርግ ሥርዓት የነበረው የደኅንነት አሠራር ምን ይመስል ነበር?” በሚል የመንደርደሪያ ጥያቄ ኦታዋ ካናዳ ነዋሪ ከሆኑ አንድ የቀድሞ ከፍተኛ የደኅንነት ባለ ሥልጣን ጋር በእሁዱ የራዲዮ መጽሔት የተጀመረ ተከታታይ ወግ፤ ደርግንና እርሱን የተከተለውን ኢህአዴግን፤ እንዲሁም በሽግግር ላይ ያለውን አዲስ አስተዳደር ያለፉ ጥቂት ወራት አሠራሮች፣ ይዞታና ቀጣይ ገፆች መልከት ያደርጋል።
እንግዳችን አቶ ጌታቸው ተፈራ በዘመነ ደርግ የደኅንነት ሚኒስትሩ የቅርብ ረዳትና የጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩ ናቸው። የያኔው የደኅንነት አሠራር ምን ይመስል እንደ ነበር ለጥያቄዎቻችን ቀጥታና ግልፅ መልሶችን በመስጠት ያወያዩን አቶ ጌታቸው፤ በርካታ ዓመታት በዘለቀው በቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥትና በጊዜው ይታገሉት በነበሩት አማፅያን ኃይሎች ማካከል .. (ዘግይቶም ዋነኞቹ ሁለቱ የኢትዮጵያንና የኤርትራን መንግሥታት ለመመስረት ይበቃሉ) የተካሄደውን ውጊያ ውጤትና ፍፃሜ፤ በተለይም ከደኅንነት መሥሪያ ቤቱ አቋምና ሥራ አንፃር ለመመርመር የሚጥሩትን ጥቄዎች ይመልሳሉ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ