በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣይቱ ቃጠሎ


ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ
ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ

ከ1898 ዓ.ም ጀምሮ መሃል አራዳ ላይ ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ የቆመው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሆቴል የደረሰበት ቃጠሎ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ አስቆጭቷል፡፡

ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ
ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከ1898 ዓ.ም ጀምሮ መሃል አራዳ ላይ ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ የቆመው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሆቴል የደረሰበት ቃጠሎ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ አስቆጭቷል፡፡

ቃጠሎው የተነሣው ዕሁድ፤ ጥር 3 / 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን በእቴጌ ጣይቱ በተከፈተው ታሪካዊ ሆቴል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

ሆቴሉ ውስጥ ክፍሎች ይዘው የነበሩ የውጭ እንግዶች ለቅቀው ወጥተዋል፡፡

በቅድሚያ የተረባረቡት ሰው ላይ ጉዳት እንዳይደርስና እሣቱን ማጥፋት ላይ መሆኑን የገለፁት የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ኮማንደር ጋሻው ፅጌ የቃጠሎውን መንስዔ እያጣሩ መሆኑን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ
ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ

ቃጠሎው በሰው ላይ ጉዳት አለማድረሱ ታውቋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG