ማርቲን ሸበየና ዮሀን ፐርሶን የተባሉት በኢትዮጵያ የተከስሱ ስዊዲናውያን ጋዜጠኞች አሻብሪዎችን በመርዳትና የሀገርን ሉአላዊነት በመድፈር ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ የጥፋተኛነት ውሳኔ ያሳለፈው የጋዜጠኛነት ሙያቸውን እንደ ከለላ ተጠቅመው በኢትዮጵያ መንግስትና በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ የኦብነገን የሽብር አላማ በመደገፍ ራሳቸውን እንደታጣቂ በማዘጋጀት የሀገሪቱ የነዳጅ ሀብት ያለበትን ቦታ ቁፋሮ የፕሮጀክቱና የመከላከያ ሀይል ቁርኝትና የጥበቃ ሁኔታን ያጠኑና የኦብነግን የሽብር አላማ ለማሳካት እየተንቀሳቀሱ ሳሉ በቁጥጥር የዋሉ በመሆናቸው ለአሸባሪ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ተግባር ተሳትፈዋል በሚል ነው።
የቅጣት ውሳኔ ለመበየን ደግሞ ተለዋጭ ቀጠሮ ተስጧል።