በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኻርቱም ስምምነትና ኅዳሴ ግድብ


የኅዳሴ ግድብ ማሣያ
የኅዳሴ ግድብ ማሣያ

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሰሞኑን ኻርቱም ላይ የተካሄደው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውኃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ኅዳሴ ግድብ ላይ ለተነሱ ውዝግቦች ከሰማንያ አምስት ከመቶ በላይ መልስ ሰጥቷል ሲሉ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር መናገራቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ሦስቱ ሃገሮች ተቋርጦ የቆየውን ምክክራቸውን እንደገና ባደሱበት በዚህ ስብሰባ ማብቂያ ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

“ኢትዮጵያ በግድቧ ላይ ተጨማሪ ጥናቶችን እንድታካሂድ የሚያሳስብ መልዕክት አዝሏል” ያሉትን ዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ሃሣቦች ተቀብለው ለመተግበር መስማማታቸውንና ይህንኑም የስምምነት ሰነድ ትናንት መፈረማቸውን የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ዶ/ር ሁሣም አል ማግሃዚ የነገሩት መሆኑን አል ጣህሪር የሚባለው ሃገሪቱ ውስጥ የሚሠራጨው የግል ቴሊቪዥን ጣቢያ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ጥናቶቹን ማካሄድ በሚቻልባቸው የአፈፅፀም ዘዴዎች ላይም መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG