በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ያሉ ባለሃብቶች


የኢትዮጵያን ግዛት “ጥሶ ገብቷል” ላሉት የሱዳን ጦር ጉዳይ መንግሥት መፍትኄ እንዲሰጥ በአካባቢው ነዋይ ያፈሰሱ ባለሃብቶች ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት የሚደገፍ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ “የሱዳን ጦርን አስለቅቋል” የሚባለውም እውነት አለመሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

መተማ ዮሐንስ ላይ በ1300 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችን አልምተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ አደራጀው አስማማው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም. ሰብሉን በመሰብሰብ ላይ እንዳሉ በሱዳን ሠራዊት አካባቢው መወረሩን አስታውሰዋል።

የሱዳን ጦር የእርሻ ማሳቸውን የወረረው ሥፍራው ላይ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለቅቆ በወጣ በሁለተኛው ቀን እንደነበረ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ያሉ ባለሃብቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:21 0:00


XS
SM
MD
LG