በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት:- ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማግስት


Panelists: discuss a way forward - post State of Emergency Ethiopia
Panelists: discuss a way forward - post State of Emergency Ethiopia

“ተጠያቂነትን አልተማርንም። ለሞቱት ሰዎች የተጠየቀ ሰው የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲህ ያሉት የጭፍን አሰራሮች ተቁዋሞቻችንን ይገድሏቸዋል።” አቶ የሺዋስ አሰፋ። “ሰው እኮ አንዴት ነው ያለመቀበሉን ሃሳቡን የሚገልጽበት መስመር መኖር አለበት። ሰው በተናገረ ቁጥር እንደ ጠላት ማየት የመንግስትነት አያያዝ ነው ብዬ አላምንም ።” ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ። “የመንግስት ተቀባይነት በምን ላይ ነው የሚመሰረተው? እነኝህን ችግሮች ፖለቲካዊ ገፅታ በዚህ መንገድ እፈታቸዋለሁ’ ማለት አልቻለም።” አቶ ሙልጌታ አረጋዊ።

አነጋጋሪው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀ ማግሥት በሕዝቡ ዘንድ ከተፈጠረው ስሜት የሚነሳው ውይይት፤ ከአዋጁ ባሻገር የአገሪቱን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ይዞታ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ይመረምራል።

የአዋጁን ሕጋዊ መሰረት፣ የዜጎችን መብት ጥበቃና ይልቁንም ደግሞ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩትን ግጭቶች እና የሚያስከትሉትን አደጋ የመከላከል ግዴታ እና አስፈላጊነት በትይዩው ይመለከታል።

ተወያዮች:- ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ፤ እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የOld Dominion University የPublic Management and Public Policy መምሕር እና የግጭት አፈታት ባለ ሞያ፤

አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፤ የሕግ ባለ ሞያ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕገ መንግሥት እና የመገናኛ ብዙሃን ህግ መምህር እንዲሁም፤

በዩናይትድ ስቴትሷ የዋሽንግተን ሲያትል ከተማ በተካሄደው አገራዊ ጉባኤ ለመሳተፍ ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡት የሰማያዊ ፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ናቸው። የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:13 0:00
ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:25 0:00
የውይይቱን ሶስተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:34 0:00
የውይይቱን አራተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:51 0:00
የተከታታይ ውይይቱን የመጨረሻ ክፍል እነሆ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:21 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG