በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፈጉባዔ አባዱላ ስለመረጃ ነፃነት ተናገሩ


አባዱላ ገመዳ - የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ /ፎቶ - ፋይል/
አባዱላ ገመዳ - የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ /ፎቶ - ፋይል/

የመረጃ ነፃነት የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥና ሌሎች መብቶች መከበር መሣሪያ እንደሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ አሳስበዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

መገናኛ ብዙኃን መረጃ በሚፈለገው ደረጃ መሰብሰብ እንዲችሉ የአስፈፃሚው ክፍል ሥር የሰደደ ምሥጢራዊነት መሠበር እንደሚኖርበት አፈ ጉባዔው ተናግረዋል፡፡

አፈጉባዔ አባዱላ ሂልተን ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው “የመረጃ ነፃነት ሕግ አፈፃፀምና ተግዳሮቶቹ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የውይይት መድረክን ሲከፍቱ የመረጃ ነፃነት ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ያለውን ጥቅም አብራርተዋል፡፡

“መረጃ የማግኘት መብት የግልፅነትና የተጠያቂነትን መርኆች የሚያጎለብትና የሕዝብ ተሣትፎንና የሥልጣን ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ መልካም አስተዳደርን የማጠናከር ዓላማ ስላለው ሁለቱም የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው” ብለዋል አፈጉባዔው፡፡

መንግሥት በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ዘመን በዋነኛነት ከያዛቸው አጀንዳዎች አንዱ ይኸው የመልካም አስተዳደር ጉዳይ እንደሆነም አቶ አባዱላ ገልፀዋል፡፡

ይህንን አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ በመረጃ የታጠቀ፣ የነቃና ለመብቱ ተሟጋች የሆነ ዜጋ ማፍራት ግዴታ መሆኑንም አፈጉባዔው አስገንዝበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG