የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከብት ዘርፈዋል የተባሉ 44 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮችን ማሰሩን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ከ200 በላይ ከብቶችን ማስመለሱንና ለባለቤቶቹ ማስረከቡንም ፖሊስ ገልጿል።
ባለፈው ዐርብ ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ ተይዘውበት ከነበረው ሱርማ ወረዳ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከል መዘዋወራቸውንም የኮሚሽኑ ሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም