በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ፣
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ፣

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ኢትዮጵያ እራሷን ከሶማሊያ ከገነጠለቸው የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባህር በር ስምምነት ምክንያት አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ውዝግባቸውን ለመፍታት ትላንት ረቡዕ ተስማምተዋል፡፡

በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ሸምጋይነት የተካሄደውን ሦስተኛ ዙር ድርድር ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መህሙድ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ተስማምተዋል።

“የአንካራው ስምምነት” ተብሎ በተሰየመው ስምምነት መሰረት፣ “የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላው ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገውን የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር እና የአፍሪካ ኅብረት ድንጋጌዎችን ለማክበር እና ለዚህም ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ” ተስማምተዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00

መግለጫው አክሎም ፣ “በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አወዛጋቢ ጉዳዮችን በመተው እና በመተጋገዝ የጋራ ብልጽግናን ለማስፈን በትብብር ለመቀጠል ተስማምተዋል” ብሏል።

“ሶማሊያ በአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ትሰጣለች። የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የግዛት አንድነትን በማክበር ከተረጋገጠው የኢትዮጵያ የባህር ተደራሽነት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ሊገኙ እንደሚችሉ አምነዋል።” ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ተቀራርበው በመሥራት የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የንግድ ሥርዐቶች በሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት፣ የኮትንራት፣ የኪራይ እና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ጨምሮ በሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ሥልጣን ሥር የኢትዮጵያ ፌደራል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ከባህርና ወደ ባህር የሚያደርስ በር ተደራሽነት ለማረጋገጥ ተስማምተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገሮች “እኤአ በየካቲት 2025 መጨረሻ በቱርክ አመቻችነት በአራት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ለመፈረም ዝርዝር የአፈጻጸም ነጥቦች ላይ የሚደረገውን ድርድር በቅን ልቦና ለመጀመር ወስነዋል” ሲል መግለጫው ገልጿል። ስምምነቱን ያደራደሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ሁለቱን ወገኖች አድንቀዋል።

/በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG