በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ከፀሐይ ኃይል 500 ሜጋዋት ማመንጫ ለመገንባት ተስማሙ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዚዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አቡዳቢ በአል ሻቲ ቤተመንግሥት እአአ 1/17/2023
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዚዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አቡዳቢ በአል ሻቲ ቤተመንግሥት እአአ 1/17/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ ከኢሚሬትስ የታዳሽ ኃይል ኩባኒያ ማስዳር ጋር በፀሐይ ኃይል 500 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ሥምምነት መፈረሙን አስታውቀዋል።

ሥምምነቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቁልፍ የኢንዱስትሪ ግንባታ ትልም በሆነው መሰረት የኢትዮጵያን የኤነርጂ አቅም በከፍተኛ ደረጃ ሊያሳድግ እና የኤነርጂ ምንጮቹን አይነት ለማስፋፋት የሚጠቅም እንደሚሆን ሮይተርስ ዘግቧል።

የፀሐይ ኃይል ኤነርጂ ማመንጫ ጣቢያው በምን ያህል ወጪ እንደሚገነባም ሆነ የት እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝርዝር እንዳላሳውቁ ሮይተርስ አመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ቢል ለኔ ስዩምም ሆነ ከኤሚሬትሱ ማስዳር ኩባኒያ ማብራሪያ ማግኘት እንዳልቻለ ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG