በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የምልክት ቋንቋ ትምህርት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተማሪዎችን እያገኘ ስላልሆነ፣ በስልጠናው ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ "ችግሩ በምልክት ቋንቋ ዕድገት ላይ ችግር ይፈጥራል፣ መስማት የተሳናቸው ዜጎች አገልግሎት እንዳያገኙም ያደርጋል" ብለዋል፡፡ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ መስማት የተሳናቸው ዜጎች በአገልግሎት ተቋማት የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ገልፆ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት እየተዘጋጀ መኾኑን አመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም