አገራቸው በቀጣዩ የበጀት አመት ጠቅላላው የሃገር ውስጥ አማካይ ምርቷ የ2 ነጥብ 1 በመቶ ማዘቅዘቅ ይገጥመዋል ሲሉ የኢትዮጵያው የገንዘብ ሚንስትር አህመድ ሺዴ በዛሬው ዕለት አስታወቁ።
ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ለሁለት አመት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና አስከፊ የአየር ንብረት መዛባት የፈጠሩትን ተደራራቢ ፈተና ጨምሮ የሃገሪቱን የምጣኔ ሃብት ይዞታ ካዛቡ በርካታ ሁኔታዎች በማገገም ላይ መሆኗ ተጠቅሷል። ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ረጅም ጊዜ የዘለቀ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ከከሰቷቸው ብርቱ ፈተናዎች ጋር በመታገል ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ባለፈው የታሕሳስ ወር የእዳ ክፍያዋን በማቋረጥ በበርካታ አመታት ውስጥ ሶስተኛ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ አይዘነጋም።
እነኝህ ሁሉ ፈተናዎች ባሉበት በመጭው የበጀት አመት በያዝነው አመት ከተዘገበው የ7 ነጥብ 9 በመቶ ወደ 8 ነጥብ 4 በመቶ የሚያንሰራራ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚዘገብ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ቅርብ አመታት ውስጥ በርካታ ማሕበራዊ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ገጥመዋታል’ ያሉት አቶ አህመድ አክለውም “እነኝህን ፈተናዎች ለመወጣትም የተለያዩ የተሃድሶ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብለዋል። አያይዘውም የሚቀጥለው አመት የሃገሪቱ ገቢ ከውጭ እርዳታ የሚገኘውን ጨምሮ 612 ቢልዮን ብር ይደርሳል’ ብለዋል።
በአንጻሩ የሚቀጥለው ዓመት የሃገሪቱ በጀት 972 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር እንደሚጠጋ ጠቁመው፣ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጻር የሃያ አንድ በመቶ ጭማሪ መሆኑ ዘርዝረዋል። መንግስት በአመቱ ቅድሚያ የሰጣቸው እቅዶችም የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን መቅረፍ እና አገሪቱ ያለባትን እዳ ጤናማ ከሚሰኝ ደረጃ ማድረስ፤ እንዲሁም የእዳ ክፍያዎች ማመጣጠን ነበሩ ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ‘ብድር ለማግኘት ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ጋር በመደራደር ላይ ያለችው ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም በከፍተኛ መጠን ዝቅ ለማድረግ ትስማማ ይሆናል’ ሲሉ ተንታኞች ግምታቸውን ሰንዝረዋል።
መድረክ / ፎረም