የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ የውጭ የኢንቨስትመንት ባንኮችን ለማስገባት ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶክተር ዳኪቶ ዓለሙ፣ ፈቃድ ያገኛሉ የተባሉት የውጭ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ከተለመዱት የንግድ ባንኮች የተለዩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡ መንግሥት አስፈላጊውን የቁጥጥር ሥራ ለማከናወን የሚያስችለው ዝግጅትም ሊኖረው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው አቶ ይርጋ ተስፋየ ደግሞ፣ በፋይናንስ ዘርፍ የተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ፣ እንደ ውጭ ምንዛሬ እጥረት ያሉ ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የመፍታት የአጭር ጊዜ ግብን ታሳቢ ካደረገ፣ ሀገራዊ ጉዳትን እንደማያስከትል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በንግድ ባንክ ዘርፍ ለሚሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ፣ ለመንግሥት ብዙኀን መገናኛዎች ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡
መድረክ / ፎረም