በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲቦር ናዥ፣ ማይክ ራይነር በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ


የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ እና ኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር
የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ እና ኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ግብ ወጊያው ፈጥኖ እንዲቆም፣ ሰላም እንዲመለስ፣ የሲቪሎች ደኅንነት እንዲጠበቅ መጣር መሆኑን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ አስታውቀዋል።

ትግራይ ክልል ውስጥ ባለው ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር ጋር ሆነው ትናንት መግለጫና ለጋዜጠኞች ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ቲቦር ናዥ “የህወሓት መሪዎች ግጭቱን ዓለምአቀፍ ገፅታ ለማስያዝ እየጣሩ ናቸው ሲሉ ከስሰዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ “እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሊደርስ የሚችል ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተሰድደው ሱዳን ሊገቡ ይችላሉ” ብለው እንደሚጠብቁ አፋጣኝ ዓለምአቀፍ ድጋፍ እንዲደርስላቸው የጠየቁት በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ለህፃናት ደራሽ ተቋም /ዩኒሴፍ/ የሱዳን ተጠሪ ተናግረዋል።

ሱዳን ውስጥ ያለው የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሁኔታ ደግሞ “ሙሉ ሰብዓዊ ቀውስ ነው” ብለዋል በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ባባር ባሎች ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ቲቦር ናዥ፣ ማይክ ራይነር በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:27 0:00


XS
SM
MD
LG