ባለፈው ሳምንት ማብቂያ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በዩናይትድ ስቴይስትስ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር። በጸጥታ ጥበቃ፣ አስተዳድርና የንግድ ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ፤ የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ያብራሩልናል።
አዲሱ የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ደግሞ ከአዲስ አበባ ለአሜሪካ ድምጽ በተለይ የሰጡትን ቃለ-ምልልስ ይዘናል።
በቅድሚያ በኮንግረስ የቀረበ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ 128 ን በተመለከተ፤ የአሜሪካውን አምባሳደር ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን አዘጋጅቷል።
በጸጥታና ደህንነት ይዞታ የዩናይትድ ስቴይትስ አይነተኛ አጋር የሆነችው ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ይዞታዋ ትተቻለች። ኢትዮጵያ ከዚህ በተጨማሪም ከአሜሪካ ጋር የንግድ ግንኙነቷን ለማጠናከር ትፈልጋለች።
የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከዩናይትድ ስቴይስ ሬክስ ቴለርሰን ጋር ለመወያየት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መጥተው ነበር። ሌሎች የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙበትን ጉባዔ አስመልክቶ ቃል አቀባያቸው አቶ መለስ ዓለም የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዩናይትድ ስቴይትስ ኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ የቀረበው ረቂቅ ውሳኔ 128 “በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ክብር የቆመ ሁሉን አቀፍ አስተዳድር እንዲሮን ለመደገፍ” ይላል በመቅድሙ። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የሚታዩ ያላቸውን የመብት ጥሰቶችና የዴሞክራሪያ አስተዳድር በደሎች የሚዘረዝርና በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተፈጸሙ ያላቸውን የመብት ጥሰቶች በማውገዝ፤ የማስተካከያ ፍትሃዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይጠይቃል።
በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት አቋም ምንድን ነው? አቶ መለስ ዓለም፤ የውጭ ጉዳይ ምንስቴር ቃል አቀባይ ያብራራሉ።
ኢትዮጵያ ከሳውዲ ጋር ያላት ግንኙነትና ከኳታር ጋር እየጠነከረ የመጣው ግንኙነት
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላቸውን ሼክ ሞሀመድ አል አሙዲ በቁጥጥር ስር አውላለች። በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችም እንዲወጡ ሪያድ በተደጋጋሚ የጊዜ ገደቦች ስታወጣና ስታስፈጽም ቆይታለች።
በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያና የሳውዲ ተቀናቃኝ ካታር ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክረዋል። በያዝንው ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ኋይለማርያም ደሳለኝ የተመራ ልዑካን ቡድን በኳታር ጉብኝት አካሂዷል።
ሁኔታውን እንዲያስረዱን አቶ መለስ ዓለም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ያስረዳሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ