አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ሣዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ “ተፈፅሟል፣ እየተፈፀመም ነው” ያለውን ግፍ በመቃወም ዕሁድ፤ ኅዳር 8/2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
የሰልፍ ዕውቅና የሚሰጠው ክፍል ግን በቃል አሉታዊ መልስ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ፡፡
አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አቅራቢያ በተሰባሰቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ “ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እሥር ተፈፅሟል” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ድርጊቱን አውግዟል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል ሰልፉ “ሕገወጥ ነው” ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አዘጋጆቹ “ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ አላገኙም” ሲሉ ለፈረንሣይ የዜና ወኪል የተናገሩት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሺመልስ ከማል ክሥ እንደሚመሠረትባቸው አመልክተዋል፡፡
የሰልፉ አዘጋጆች በኢትዮጵያዊያን መካከል “ፀረ-አረብ ስሜት እያነሣሱ ነበር - ያሉት ሚኒስትር ደኤታው - ሰልፉ ሕገወጥ በመሆኑ ፖሊስ አግባብ ያለው እርምጃ ወስዷል” ብለዋል፡፡
መለስካቸው አምሃና እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ያስተላለፏቸው ዘገባዎች አሉ፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡