በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንቷ የኢትዮጵያ ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ በድጋሚ ጠየቁ


ፕሬዚዳንቷ የኢትዮጵያ ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ በድጋሚ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

ፕሬዚዳንቷ የኢትዮጵያ ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ በድጋሚ ጠየቁ

በትውልድ የሚዘከር ሥራ ለመሥራት ከዓድዋ ልንማር ይገባል፤ ሲሉ፣ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

“የዓድዋን ዐይነት ዝክር የማናገኝበት ጎዳና ላይ ገብተናል፤” ሲሉ በአገሪቱ እየታዩ ያሉ ግጭቶችን መቀጠል የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፣ “ወንድም ወንድሙን የሚገድልበት የእርስ በርስ ግጭት በንግግር እንዲፈታ” በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው፣ የአንድነት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ርእሰ ብሔሯ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፣ በአዲስ አበባ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ትላንት በተመረቀበት ወቅት ነው።

ግጭትን በሰላማዊ ንግግር የመፍታት መፍትሔ እስከ አሁን በኢትዮጵያ ሊተገበር ያልቻለው፣ “የአገሪቱ የፖለቲካ ባህል በአሸናፊ እና ተሸናፊነት ላይ የተመሠረተ በመኾኑ ነው፤” ሲሉ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ጸጥታ ጥናቶች መካነ ጥናት ዲሬክተር እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ስለመፍትሔውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG